ዶ/ር ቴድርዎስ አድሃኖም የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክቶር በመሆን ተመረጡ፡፡

ለዛሬ አንድ ወግ ያው እንግዲ ከፌስቡክ ላይ አግኝተናል!! እናካፍላችሁ፡፡ እናንተም ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ ሼር በማድረግ አካፍሉ!!

ከዛሬ ስምንት ዓመት በፊት አንድ መላ ዓለምን ትኩረት የሳበ ፤ በዓለም አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እውን የሆነበት ለመላ አፍሪካውያን ብቻም ሳይሆን ለመላ ጥቁር የዓለም ህዝቦች የደስታ እምባ ያራጨ ክስተት ከወደ ሰሜን አሜሪካ ተደመጠ። በደም ሀረጉ አፍሪካዊ የሆነ ትውልደ አሜሪካዊ ባራክ ሁሴን ኦባማ የመጀመሪያው ጥቁር የአሜሪካ ፕረዝደንት ለመሆን ያቀደው ህልሙ ብቻ አልነበረም የዓለም ልዩ ክስተት ያደረገው። ዓለማችን በዘረኝነት ግዞት ተጠፍንጋ በጥቁር እና ነጭ የቆዳ ልዩነት ብቻ መገለልና መድሎ ተንሰራፍቶ የነበረው የጥላቻ መጋረጃ በድንቅ መከባበር እና ከልብ በመነጨ ፍቅር የከለር ልዩነት አሳፋሪው ታሪክ ማብቂያው የሆነበት በአዲሱ ትውልድ ያለፈው አስቀያሚው የዘርኝነት ታሪክ ከታሪክ ድርሳናት ሳይወርድ እዛው ታሪክ ብቻ ሆኖ እንዲቀር መላ የዓለማችን ህዝብ በልባቸው ፅላት በታተመ የቃል ኪዳን ሰነድ ለመጪው ትውልድ የተበረከተ ታሪካዊ ክስተትም ስለነበር ነው። በወቅቱ መላ ዓለም ለማመን ተቸግሯል። በሌላ በኩል ማን ያቃል የዓለም ታሪክ ይቀየራል የሚል እምነት የሰነቀ መላ ለውጥ ናፋቂ ሀይል ይህን ታሪካዊ ድል ለማጣጣም እልህ በተሞላበት የተነቃቃ መንፈስ የማያባራ ትግሉን ወድሯል። ሁሉም አፍሪካዊ የማንነቱ ጉዳይ እንቅልፍ ነስቶታል። ድሉ በነጮች ላይ የበላይነትን ለመቀዳጀት ሳይሆን በዘረኛ እና ፅንፈኛ ነጮች አስተሳሰብ ብቻ የተነፈገንን የእኩልነት መንበር ለማስከበር እንጂ። ያለአግባብ የበታች የሆንበት ታሪክ ተቀይሮ በአግባብ እኩል መሆን የምንችልበት የታሪክ ሽግግር ዕውን ሊሆን ግድ ይለዋል። ለዚህም አፍሪካውን በያሉበት የት ፣መች ፣እንዴትና ምን ማድረግ እንዳለባቸው የጋራና የግል ዕቅድና ስትራቴጂ ነድፈዋል። ለተግባራዊነቱም ከነጭ ወንድሞቻቸው ጋር መከፈል ያለበትን ዋጋ ለመክፈል ተሰናድተዋል። እንግዲህ ጉዳዩ የባራክ ኦባማ ብቻ አልነበረም።በብቃትና ችሎታ የሚያምኑ ነጭ ወንድሞቻችንና መላ የዓለም ጥቁር ህዝቦችም እንጂ። መላ አሜሪካውያን ይህችን ልዩ ቀን ሳያይዋት ላለመቅረት ፈጣሪን መማፀናቸውን ተያይዘዋል። አው በዚች ቀን የመምረጥ ዕድል የሌላቸው ሁሉ በመላ ዓለም ውጤቱን ለማወቅ አይናቸውና የቴሌቪዥን መስኮት ተጋትረዋል። BBCና CNN ነጩ እጩ የ62 አመቱ ጆን ማኬን በከፍተኛ ነጥብ እየተመሩ መሆኑን ይፋ አደረጉ ። መላ አሜሪካውያን የሚወዷትን የሀገራቸውን ሰንደቅ አንግበው ሊቆጣጠሩት በማይችሉት የእምባ ሻምፓይን እየተራጩ ጡቁሮች በነጮች ፤ነጮች በጥቁሮች አንገት ለይ ተጠመጠሙ፤ ለይፋቱ ተዋኻዱ። በድንገት የናፈቁት እንግዳቸው ከውድ ባለቤቱና ከሁለት ልጆቹ ጋር ተከሰተ ። በታላቅ ግርማ ሞገስ ምድርን በሚያናውጥ በማያባራ ሞገደኛ፤ በሚያምሩ ጥቁርና ነጭ እጆች ህብር ጭብጨባ የቺካጎ ምድር ተናወጠች። ሁለችንም በያለንበት በደስታ እምባ አዲሱን ታሪካዊ ክስተት አጣጣምነው። እነሆ አፍሪካውያን በአዲስ ታሪክ በዓለም በድንቅ ልጆቻችን ብቃት ከአዳዲስ ታሪካዊ ክስተቶች ጋር አሁንም አልተላቀቅንም። ለመጀመሪያ ጊዜ በጄነቫ የመላ ዓለም ጥቁርና ነጭ መሪዎቻችን የከለራቸውን ልዩነት በፍቅር አዋህደው ጥላቻን ሚያስረሳ አንድ ጀግና በመምረጥ የዓለምን ጤና ተቋም የለውጥ ማርሽ ሊያስቀይሩ ደምድማዋል። እኛ ኢትዮጵያውያን በመላ ዓለም የምንታወቅበት በዘመናት ሁሉ ሳይሻር ሳይገሰስ ተከብሮ ለትውልድ የዘለቀ አንድ ህግ አለን ። ይኻውም ኢትዮጵያ ስም ሲነሳ አብሮ የመቆም። ይህ መለያችን እንኳን የኢትዮጵያዊ የመላ ጥቁር ህዝብ አቋም ወደ መሆን ተሸጋግሯል። ምናልባትም ልዩነት ካለም አስታራቂ ሽማግሌ አንሻም። የእምዬ ኢትዮጵያ ስሟ ሲነሳ ልዩነቱ ወደ አንድነት ከብርሃን ፍጥነት በላቀ ፍጥነት ይቀየራል። ለዚህም ነው መላ አፍሪካ ከካይሮ እስከ ኬፕታውን፤ ከዳካር እስከ ናይሮቢ ለኢትዮጵያዊው ጀግና ዶ/ር ቴድሮስ አንድ ድምፅ በማሰማት ዓለምን ያስደመሙት። ኢትዮጵያውያን አንድነታችን በታሪክ ብቻ ሳይሆን አሁንም ትውልድ ተሻጋሪ መሆኑን ለዓለም እረጋግጠናል! ያኔ በጀግናችን አቤ (አበበ ቢቂላ) በሮም የተሰራው ጀግንነት አሁን በጀግናው ቴዲ ፫ኛ (ቴድርዎስ አድሃኖም) በጀኔቫ ተደገመ።

ሠላም እና ስኬት ለጀግናው ልጃችን፤ ለወከላት ሀገራችን፤ ለምንወዳት አህጉራችን! በአጠቃላይ ለአለማችን!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ! የምትወዷቸው ላይክ እና ሼር!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *